Skip to main content

The Service Announces Procurement Worth 13.6 Billion Birr in Six Months

አገልግሎቱ  በስድስት ወራት በ13.6 ቢሊዮን ብር ግዥ መፈፀሙን አስታወቀ

ዜና፣ አዲስ አበባ፣ የካቲት 26 ቀን 2018  ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት ከፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች እና አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በዛሬው ዕለት የጋራ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩም የሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዘዳንቶችና ምክትል ፕሬዘዳንቶች፣ የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የስራ ኃላፊዎች፣ የአቅራቢ ድርጅት ባለቤቶች፣ የአገልግሎቱ አመራርና ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡  

መድረኩን በይፋ የከፈቱት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ እንዳሉት በተያዘው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ለሁሉም የፌደራል ባለበጀት መ/ቤቶች እና የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች አገልግሎት የሚውሉ የጋራ መጠቀሚያ ዕቃዎችንና ሌሎች ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ በመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት (e-GP) በመጠቀም በ13.6 ቢሊዮን ብር ግዥ መፈፀሙን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል አገልግሎቱ “ፅዱ ተቋምን በመፍጠር፤ ሀብትን እንፍጠር” በሚል መሪ ሃሳብ በተሰራው አገር አቀፍ ሰፊ የንቅናቄ ስራ እንዲወገዱ ወሳኔ የተሰጠባቸውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና ልዩ ልዩ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ ባለፋት ስድስት ወራት ብቻ ከ207 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ ማስገኘቱን አስታውቀዋል። ይህም ገቢ በአገልግሎቱ ታሪክ በስድስት ወራት ከንብረት ማስወገድ የተገኘ ትልቁ ገቢ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል፡፡ 

አቶ አስማረ አክለውም አገልግሎቱ በመንግስት የተሰጠውን ትልቅ ኃላፊነት በተሻለ ብቃትና አቅም ለመወጣት እና የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ፣ ውጤታማ ፣ ግልፅና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን እንደ ሀገር የታቀደውን ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዕቅድ መነሻ በማድረግ የራሱን “Digital PPS” ዕቅድ በማቀድ ስራዎችን ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና ዲጅታላይዝ በማድረግ እንዲሁም የጀመረውን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን በአጽኖት ተናገረዋል፡፡

በአገልግሎቱ የግዥ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ወርቁ ገዛኸኝ  በግማሽ ዓመቱ በግዥ፣ ውል አስተዳደርና  ንብረት ማስወገድ ዋና ዋና አፈጻጸሞች እና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ በማተኮር ለውይይት መነሻ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን በአገልግሎቱ  የበላይ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

The Service Announces Procurement Worth 13.6 Billion Birr in Six Months

News, Addis Ababa, March 5, 2026 (Yekatit 26, 2018 E.C.)

The Public Procurement Service held a joint consultation forum today with federal budget institutions and supplier organizations.

The forum was attended by presidents and vice presidents of all government universities, heads of federal budget institutions, owners of supplier organizations, as well as the leadership and staff of the Service.

Opening the forum officially, the Director General of the Service, Honorable Mr. Asmare Yigezu, stated that during the first six months of the current fiscal year, procurement worth 13.6 billion Birr was carried out using the government Electronic Government Procurement System (e-GP). The procurement covered common-use goods and other strategically important items required by all federal budget institutions and government universities.

On the other hand, the Service also announced that under the national initiative carried out with the slogan “Create a Clean Institution; Let Us Build Wealth,” more than 207 million Birr was generated for the government over the past six months through the sale and disposal of used vehicles and various other assets that had been decided for removal. The Director General noted that this revenue represents the largest amount generated from asset disposal in a six-month period in the history of the Service.

Mr. Asmare Yigezu further emphasized that the Service is working with strong commitment to fulfill the significant responsibility entrusted to it by the government with greater efficiency and capacity. In order to make service delivery fast, effective, transparent, and accountable, the Service has developed its own “Digital PPS” plan, aligned with the national Digital Ethiopia 2030 strategy. Through this plan, the Service aims to fully support its operations with technology, digitalize its activities, and successfully implement the ongoing government service and administrative reform.

The Chief Executive Officer for Procurement at the Service, Mr. Worku Gezahagn, presented a discussion paper focusing on the key achievements and challenges encountered during the half-year period in procurement, contract administration, and asset disposal.

Finally, questions and comments were raised by the participants, and the discussion concluded after responses and clarifications were provided by the senior leadership of the Service.

 

 

About

We are transforming procurement into a strategic instrument for sustainable economic growth.

Featured Posts

Contact info

Contact information Federal Public Procurement Service (FPPS).